Category: Religion

ኑሮ በአገርኛ÷ ጾም ይበዛበታል!

ባሕር ማዶ ካሉ ሰዎችጋ ስናወራ አንዳንድ የማይገቡን ወሬዎችን እየሰማን ጭንቅላታችንን እየናጥን “ወቸ ጉድ!” ማለታችን አይቀሬ ነው፡፡ ለኛ ባዳ ከሆነው ከቀላሉ “GPS” ጀምሮ፣ credit card ቢሉ፣ ምን ቢሉ ሁሉም ለኛ እንቆቅልሾች ናቸው፡፡ ወጉ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ እንዲሉ “GPS” ቀርቶብኝ እበላው ባገኘሁ የሚለው እስኪታወሰን ድረስ እንደመማለን፡፡ እዚህ GPS የለም፣ credit card የለም፣ ባቡር (ወይም subway station ብሎ ቋንቋ) የለም፣ smart phone የለም፣ wi-fi የለም (አለ እንዴ?) ለነገሩ የዚህ ጫወታ ጉዳዮች እነዚህ ሁሉ ስላልሆኑ እንኳን ደስ ያላችሁ፡፡ በርግጥ ግን ወደጫወታው አጀንዳ ለመድረስ አሁንም ዳር፣ ዳሩን መነካካት የግድ ነው፡፡ ‹አሜሪካኖች ለምን ወፋፍራም ሆኑ? ኢትዮጵያውያኖች ለምን ቀጫጭን ሆኑ?› ብለን ብንጀምርስ! Continue reading

የሁለት እምነቶች ጦርነት… [ወግ አጥባቂዎች እንዲያነቡት የማይመከር – ክፍል ሦስት]

ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው፡፡ ጦር ሜዳው ሕሊና፣ ጦረኞቹ አማኞች እና ኢ-አማኒዎች ናቸው፡፡ በኔ ጦማር ኢ-አማኒዎች ምክንያተኞች እንደሆኑ ይታመናል፡፡ ለዚህም ነው፣ ስለ ኢ-አማኒዎች በተናገርኩ ቁጥር ከአማኒዎች ጋር ማወዳደር የሚቀናኝ፡፡ እንግዲህ በክፍል ሁለት ጽሁፌ ለማመልከት እንደታገልኩት አማኒዎች ከኢ-አማኒዎች አንፃር (ወይም አንግል) ሲታዩ ፈሪዎች፣ ጠባቦችና አምላካችን ብለው በሚጠሩት አካል ላይ ጨካኞች መሆናቸውን ገልጬ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ‹‹ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል›› (መዝ. 14፥1) የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱሰ ጥቅስ ተንተርሼ ሙግቴን እቀጥላለሁ፡፡ ~ ‹ጎበዝ በይፋ ፈጣሪ የለም ይላል› ወደማለቱ ነኝ፡፡

ኢ-አማኒዎች (atheists) ሞራል የሌላቸውና ማስተዋል የተሳናቸው ተደርገው በአማኒዎች ይሳላሉ፡፡ ኢ-አማኒዎች ከአማኒዎች ይልቅ የሞራል (የሕሊና) ጥያቄን ከግምት ውስጥ ማስገባት የሚችሉና ዓለምን ለመቀየር የሚያስችል አስተውሎት ያላቸው ስለመሆናቸው ጥናቶች ሳይቀሩ ያረጋግጣሉ፡፡ Continue reading

የሁለት እምነቶች ጦርነት… [ወግ አጥባቂዎች እንዲያነቡት የማይመከር – ክፍል ሁለት]

በክፍል አንድ ጽሁፌ የፈጣሪ ሕልውናን በተመለከተ መከራከር እና የግል አቋም መያዝ እንጂ መደምደሚያ ላይ መድረስ እንደማይቻልና በሳይንሳዊ ሙግት የፈጣሪን ሕልውና (የቅዱሳን መጽሃፍትን ፍፅምና) ማረጋገጥ እንደማይቻል በጥቂት ነጥቦች መግለፄ ይታወሳል፡፡ ዛሬ ደግሞ ቃል በገባሁት መሰረት ጥቂት ስለዝግመተ ለውጥ እና ኢ-አማኒነት ለመነጋገር የሚያስችሉንን ነጥቦች ይዤ ቀርቤያለሁ፡፡
ጥቂት ስለዝግመተ ለውጥ
በዝግመተ ለውጥ (evolution) እሳቤ ላይ ብዙ ተሳልቆዎች ተነግረዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ስላቆች የተነገሩት ባላዋቂነት መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ከቀልዶቹ መካከል አንዱን አንስተን ጥቂት እንነጋገርበት፡፡ አባትና ልጅ እያወሩ ነው፡፡
ልጅ፡- አባዬ፤ ሰው ከየት ነው የመጣው?
አባት፡- እኛማ የአምላክ ፍጡሮች ነን፤
ልጅ፡- አስተማሪያችን ግን ሰው ከዝንጀሮ ነው የመጣው ብሎ ነገረን፤
አባት፡- እንግዲህ እሱ አባቱ ዝንጀሮ ይሆናል፤ እኔና አንተ ግን የአምላክ ፍጡሮች ነን፡፡
ቀልዱ ሊያስቅ ይችል ይሆናል እንጂ መሰረታዊ ችግር አለበት፡፡ ምክንያቱም የዝግመተ ለውጥ እሳቤ ሰው ከዝንጀሮ መጣ አይልም፡፡ የዘንድሮ ሰው እና የዘንድሮ ዝንጀሮ አንድ ዓይነት የዘርግንድ ነበራቸው የሚል መላምታዊ ድምዳሜ ግን ያስቀምጣል፡፡ ይሄ እንዴት ሊሆን ይችላል – ወደ መልሱ የሚያመራን ጥያቄ ነው፡፡

Continue reading

የሁለት እምነቶች ጦርነት… [ወግ አጥባቂዎች እንዲያነቡት የማይመከር]

ዓለማውያን በምክንያት ሲሟገቱ ኢትዮጵያውያን ግን ገና ‹‹የዘራፍ›› ዘመን ላይ ነን፡፡ ይህንን ለመናገር ያደፋፈረኝ በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ ትችት መሰንዘር – በሃገራችን – ቡጢ የሚያስቀምስ ሃጢያት መሆኑን ስለማውቅ ነው፡፡ እኔ ኢ-አማኒ (atheist) ነኝ፡፡ በርግጥ እንደ ብዙሐኑ ሁሉ እኔም ቤተሰቦቼ በውልደት ያወረሱኝ አምልኮታዊ አስተሳሰብ ነበረኝ፡፡ ልዩነቱ ለአቅመ መጠየቅ ስደርስ የተነገረኝን መቀበል ስላልተቻለኝ የሆንኩትን ሆኛለሁ፡፡

ዛሬ በዚህ ጽሁፍ ላይ ትልቁ አጀንዳ የኔ ጉዳይ አይደለም፡፡ በርግጥ እኔ ኢ-አማኒ መሆኔን መግለፅ ያስፈለገኝ – ኢ-አማኒነት ከአማኒነት የተሻለ ምክንያታዊ ነው ብዬ ስለምከራከር ነው፡፡ ማንም አንባቢ ጽሁፌ ላይ የሚመለከተውን ሐሳባዊ ወይም አመክንዮአዊ ግድፈት በአስተያየቱ ሊጠቁመኝ ወይም በትችት ሊያር’ቀኝ (ር ይጠብቃል) የመሞከር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ፈጣሪ አለ ወይስ የለም? Continue reading