Category: Politics

የእንቆቅልሹ እንቆቅልሾች

ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒልክ ሲሞቱ፣ መኳንንቱ ለሕዝቡ የ‹እምዬ›ን ሞት ለማርዳት ፈርተው ዓመታት ቆይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊስ ዳግማዊው ‹ዳግማዊ-ምኒልክ› ለመሆን በቅተው ይሆን እንዴ? ይህቺን ጽሁፍ እስካሰናዳሁባት ሰዓት ድረስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው፣ በጠና ታመዋል እና ሞተዋል የሚሉ ‹‹ታማኝ ምንጮች›› ከየአቅጣጫው እየፈለቁ ነው፡፡ እውነታውን ምሎ የሚናገር ሕዝብ ወይም የሕዝብ አባል ግን የለንም፤ ጉዳዩ በእንቆቅልሽ የተሞላ ነው፡፡

አሁን፣ አሁን ገዢው ፓርቲ የራሱ ዋሾነት ሳያንሰው የአማራጭ መረጃ ምንጮችን ታማኝነት እስከወዲያኛው ለማድረቅ ሆነ ብሎ የሚጫወተው ‹ጌም› ያለ እየመሰለኝ መጥቷል፡፡ በ‹‹ታማኝ ምንጮች›› በኩል የሐሰት መረጃዎችን ማፍሰስ፣ በጣም እስኪናፈሱ መጠበቅ፣ ወሬዎቹን በከፊል የሚያረጋግጡ መግለጫዎችን መስጠት፣ መጨረሻ ላይ ግን ወሬዎቹ በሙሉ ‹‹ከአሉባልታ›› ያልበለጡ መሆናቸውን አረጋግጦ የዜና ምንጮቹን ተአማኒነት መግደል፡፡ ለኔ፣ መለስ ቢያንስ በቅርቡ ወደቢሯቸው መመለስ ከቻሉ ተናፋሽ ወሬዎችን ለማመን ይሄ የመጨረሻዬ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ከዚያ በፊት የዚህ እንቆቅልሽ እነቆቅልሾች ስለሆኑት ነገሮች ትንሽ ልበል፡፡ Continue reading

Advertisements

የተመቻቸ ጊዜ መጠበቅ?

ኅወሓትን ለ10 ዓመታት የመሩት አቦይ ስብሃት፣ የመሪነቱን ሥልጣን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በፈቃዳቸው ካስረከቡ 23 ዓመት ሆኗቸዋል፡፡ ለአዲስጉዳይ በሰጡት ቃለምልልስ ላይ፣ አቦይ ስብሃት ‹‹የኅወሓትም ሆነ የኢሕአዴግ ሕገ-ደንብ አንድ ኃላፊ በስልጣን ላይ የሚቆይበትን ዓመት አይገድብም፡፡…›› ብለው ተናግረዋል፡፡ እውነት ነው፤ እንኳን የፓርቲው የአገሪቱ ሕገ-መንግስትም ለ‹‹ትዕምርትነት›› የሚቀመጠውን ፕሬዚደንት የስልጣን ዘመን ሲገድብ፣ የክልል ፓርላማን እስከመበተን ስልጣን የተቸረውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዘመነ መንግስት አይወስነውም፡፡

ኢሕአዴግ እንዲህ ዓይነት ነገር ይወዳል፡፡ ለምሳሌ በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 39 ላይ ‹የራስን እድል በራስ መወሰን እስከመገንጠል› ብሎ ይጽፍና ‹መገንጠል›ን ምን አመጣው ተብሎ ሲጠየቅ ‹‹ብሔር ብሔረሰቦች በመፈቃቀር እና በመፈቃቀድ አብረው የሚኖሩት የመለያየት መብት እንዳላቸው ስንነግራቸው ነው›› ብሎ ይከራከራል፡፡ በዚህ ‹‹ሕገ-መንግስታዊ አተረጓጎም›› ነው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘመነ መንግስት አለመገደብን የምመለከተው፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ (ወይም የኢሕአዴግ) የስልጣን ዘመን አለመገደቡ፣ አንድ፤ አቦይ ስብሃት እንዳሉት ‹‹…ፕሮግራሙን ማዕከል አድርጎ የጋራ አመራርን እስካረጋገጠ ድረስ…›› ችግር የለውም ለማለት ይመስላል፣ ሁለት፤ የስልጣን ዘመኑ ሳይገደብ በገዛ ፍቃዱ ይለቃል የሚል ተስፋ ይዞ ይሆናል – ልክ እንደመገንጠል/አለመገንጠሉ፡፡ ሦስት፤ የፓርቲው ሊቀመንበር ቁጭ ባሉበት የሊቀመንበሩ የሥልጣን ዘመን ይወሰን የሚል ጥያቄ ማንሳት ለአባላቱ አስፈርቷቸው ይሆናል፡፡

ስልጣንን መልቀቅ ለምን ያስፈልጋል (101)? Continue reading

እነአልበርት አይንስታይን ስለዘንድሮው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምን ይላሉ?

ስም ያለው ነገር ሁሉ ‹‹ያለ›› ነገር ነው እያለ ከልጆቹ’ጋ ሲሟገት የነበረ አንድ ጦማሪ ወዳጄ፥ ስማቸው ከመቃብር በላይ የዋለላቸው ሰዎችም ስማቸውን የሚጠሩ ሰዎች እስካሉ ድረስ ‹‹የሉም›› ማለት አይቻልም – ምክንያቱም ‹‹አሉ›› ብሏል፡፡ መከራከሪያው ለዚህ ጽሁፍ መንደርደሪያ ግብአትነት ብቁ ስለሆነ ያለምንም ክርክር ተቀብዬዋለሁ፡፡ የጨዋታዬ ርዕሰ ጉዳይ ግን ‹‹ያለ›› እና ‹‹የሌለ›› ነገር አይደለም፡፡ ይልቁንም አንዳንድ ሕያዋን ሰዎች ከተናገሯቸው ሕያው ንግግሮች መካከል እያጣቀሱ የዛሬውን የአገራችንን ፖለቲካ መሄየስ ነው፡፡ በምናባዊ ሳይንስ ሊቁ አልበርት አይንስታይን ብንጀምርስ?

1. አልበርት አይንስታይን

“The world will not be destroyed by those who do evil, but by those who watch them without doing anything.” (ዓለማችን የምትጠፋው ክፉ በሚያደርጉ ሰዎች ሳይሆን ክፉ ሲያደርጉ እያዩ ዝም በሚሏቸው ሰዎች ነው፡፡)

በኢትዮጵያ የፖለቲካ እውነታ በየጓዳው ከመንሾካሾክ እና ከመብሸቅ ባሻገር ይሄ መንግስት (ይሄ ገዢ) ያለእኛ ተገዢነት እና ፈቃደኝነት ሊጨቁነን እንደማይችል ገብቶን የተነጠቅነውን ነፃነት ለማስመለስ የምንሞክር እጅግ ጥቂቶች ነን፡፡ በተለይም ‹‹ኢኮኖሚያዊ ዕድገቱ ብዙሐኑን ስላላማከለ አንድ ቀን አገሪቱ ወደማትወጣው ችግር ውስጥ ትገባለች፣ ወዘተ. ወዘተ…›› እያሉ የጋን ውስጥ ትንታኔያቸውን የሚሰጡት ነገር ግን ለጋዜጣ እንኳን ማብራሪያ ለመስጠት ‹‹ስሜ ከተጠቀሰ አይሆንም›› የሚሉ ምሁራን ከአጥፊው ገዢው ፓርቲ ይልቅ – ለጥፋቱ ተጠያቂ መሆናቸው አይቀሬ ነው፡: Continue reading

የአንድ ኪራይ ሰብሳቢ መንግስት ታሪክ

የመንግስት መሥሪያ ቤቶች እጣ ክፍሎቼ እንዳልሆኑ እየተረጋገጠ ነው፡፡ ባለፈው ሰሞን እርሜን ‹ኢሚግሬሽን› ብሄድ ለሦስት ሰዓታት በግዞት እንደቆየሁ አጫውቻችሁ ነበር፡፡ ዛሬ ጠዋት ደግሞ የጓደኛዬን ጉዳይ ላስፈጽም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰነድ ማረጋገጫ ቢሮ ተገኘሁ፡፡ እዚህ እንደከዚህ ቀደሙ አካላዊ ጥቃት ባይደርስብኝም – መንግስታችንን በኪራይ ሰብሳቢነት እንድታዘበው የሚያደርገኝ ነገር ተከስቷል፡፡

ነገሩ ወዲህ ነው፡፡ የሰነድ ማረጋገጫ ሥራ የሚባለው ሰነዱን ባለቢሮዎቹ ተኮር ብለው ካዩት በኋላ ማሕተም ይመቱበታል – አለቀ፡፡ ይህ ሥራ የ30 ሰከንድ ሥራ ቢሆንም ብዙ ያስከፍላል – በጊዜም፣ በገንዘብም፡፡

እኔ የሄድኩት አንድ የትምህርት ማስረጃ ሰነድ ላይ የእውነተኛነት ማረጋገጫ ማሕተም ለማስመታት ነው፡፡ ይህንን ሰነድ ሌላ ቦታም ቀደም ብሎ ማረጋገጫ ማሕተም ማስመታት በቅድመ ሁኔታነት ተከናውኗል፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሰነዶች ማረጋገጫ ቢሮ ደግሞ ከግቢ ውጪ ጥቂት፣ ጊቢ ውስጥ ደግሞ በአግዳሚ ወንበር እና ከዚያ የተረፈው ግድግዳ ተደግፎ ቆሞ የተሰለፈ ብዙ ሰው አለ፡፡ ያንን መጠበቅ – በተለይ እንደኔ ላለውና በስጋ ሳይሆን ባጥንት ብቻ ለቆመ ሰው – ወገብን ይፈታተናል፡፡

በግምት ለሁለት ሰዓታት ያህል በሰልፍ ጠብቄያለሁ፡፡ ተሰልፌ ግን ስሰጋ የነበረው ስለወገቤ፣ ስለጥበቃው ወይም ከምሳ ሰዓት በፊት ወረፋው ባይደርሰኝስ ስለሚለው አልነበረም፡፡ እነዚህኞቹ እዳቸው ገብስ ነው፡፡ እኔን የጨነቀኝ ይህን ሁሉ ሰዓት ጠብቄ ያላሟላኸው አንድ ነገር አለ ተብዬ ሰልፉን እንደገና እንድጀምር ብደረግስ? Continue reading

“አሸባሪ” ፊልምም ይታገድ ጀመር

ከዚህ ቀደም ‹የባሕር በር› በሚል ርዕስ በጥላሁን ጉግሳ የተሰራው የአማርኛ ፊልም በኢቴቪ ማስታወቂያው እንዳይታይ ታግዶ የአንድ ሰሞን አወዛጋቢ አጀንዳ ለመሆን በቅቶ ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የፊልሙ ዋና ገጸ ባሕሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ‹‹በእኔ እምነት፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ አንድ ቀን መልሰው አንድ ይሆናሉ፡፡›› ብለው መናገራቸው ነው፡፡ ያለምንም ማጋነን መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ አንድ ሆነው ከሚያዩ ከሚና ሕንጻ ላይ ዓይናቸው እያየ ቁልቁል ቢወረወሩ ይመርጣሉ፡፡ የሻዕቢያን የጫካ ውለታን ኤርትራን እንደተገነጠለች በማስቀረት ነው የሚያረጋግጡት፡፡ እንዴያውም አንዳንዴ ሳስበው መለስ ከስልጣን መውረድ የማይፈልጉት ለሻዕቢያ እንደርሳቸው ታማኝ የሚሆን ኢትዮጵያዊ መተካት ስለሚከብዳቸው ይመስለኛል፡፡

ወደቀደመው ነገራችን ስንመለስ ትላንት አርብ፣ በኤድናሞል ማቲ መልቲፕሌክስ ሲኒማ መታየት የጀመረው ‘The Dictator’ የተሰኘ ፊልም እንዳይታይ ታገደ የሚል ዜና አነበብኩ፡፡ መውጣቱን ከሰማሁ ጀምሮ በጉጉት ስጠብቀው የነበረው ይህ እምባና ሳቅ ያዘለ (comedy satire) ፊልም ሦስት ቀን እንኳን እንዳይታይ በመደረጉ ለእሁዴ ሳይደርስልኝ ቀርቷል፡፡ ግን ለምን የሚለው ጥያቄ አጭር ግምቴን እንደሚከተለው አስቀምጣለሁ፡፡

በባሮን ኮኸን በገዛ ፊልሙ መሪ ተዋናይ የሆነበት ይህ ስላቃዊ ፊልም የጋዳፊ እና የሳዳም ሁሴን ድቅያ የሆነ አምባገነነዋ ገዢ ሆኖ የሚጫወት ገጸ ባሕሪ ፈጥሯል፡፡ ከፊልሙ ቅኝቶች ላይ ለማንበብ እንደሞከርኩት በርካታ የአምባገነኖች ባሕርያት የተሰገሰጉበት ይህ ፊልም፣ ከአንድ ወዳጄ እንደሰማሁት ደግሞ የኛውን ‹መለስ› ዜናዊን ቁልጭ የሚመስሉ በርካታ ትዕይንቶች አሉት፡፡ እናም የፊልሙ መታገድ ዋነኛ ምክንያት ከዚህ ውጪ ምን ሊሆን ይችላል?

በርካታ ጋዜጦች ታገዱ፣ ሰላማዊ ሰልፍ ታገደ፣ በመንግስት ያልተወደዱ ዘፈኖች በመንግስት ይዞታ ስር ባሉ ሬዲዮ ጣቢያዎች እንዳይተላለፉ ታገዱ፣ አንዳንድ መጽሃፍቶች ሜጋ መጽሃፍት ማከፋፈያ ውስጥ እንዳይገቡ ታገዱ፣ የተቃዋሚ ድረገጾችና ጦማሮች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይነበቡ ታገዱ፣ የጀርመንና የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮዎች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይሰሙ ታገዱ፣ …. ታገዱ፣ ታገዱ፡፡

እነዚህ ሁሉ ነገሮች መታገዳቸው የሚነግረን አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ ራሳቸውን ከነሞቡቱ፣ ሙአመር… (The ‘M’ Dictators) ሳይሆን ከነማንዴላ (The Democrats) ጋር ማመሳሰል ሲመኙ የነበሩት መለስ ዜናዊ፣ ሕዝባቸውን ነፃ ለማውጣት ትምህርታቸውን አቋርጠው “የነፃ አውጪ ትግል” የጀመሩት መለስ ዜናዊ፣ አምባገነንነታቸው ከተረጋገጠላቸውና የአምባገነንን መጨረሻ ከቀመሱት ሳዳም ሁሴን እና ሙአመር ጋዳፊ እንዳንዱ መሆናቸውን እርሳቸው ራሳቸውም ሆኑ የማገዱን ሥራ እየተከታተሉ የሚፈጽሙላቸው ተከታዮቻቸው ማመናቸውን ያረጋግጣል፡፡

10ሩ የድህረ-ግንቦት 20 ኪሳራዎች

ነብዩ ኃይሉ

አቶ መለስና ጓደኞቻቸው አምባገነን ስርአትን ለመቀየር ነፍጥ አንስተው፣ በጭቆና ላለመኖር ሲሉ በህይወታቸው ተወራርደዋል፤ አላማቸውን ለማሳካት ገድለዋል ሞተዋል፡፡ ድል ቀንቷቸው የዛሬ 21 አመት አምባገነኑን የደርግ ስርአት አስወግደው ምኒሊክ ቤተመንግስት ሲገቡ ኢትዮጵያን በለውጥ ጎዳና ሊመሩ፣ ዴሞክራሲን በማስፈን በሀገሪቱ አዲስ ታሪክ እንዲያኖሩ የሚያስችል ዕድል ነበራቸው ፡፡ አምባገነኑን የኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያምን ደርግ ካስወገዱ በኋላ ግን አምባገነኑን የአቶ መለስ ዜናዊን ስርአት ከማስቀመጥ ባለፈ በግንቦት 20 ድል ታሪክ ሊሰሩ አልቻሉም፡፡

ያ ሁሉ መስዋዕትነት የተከፈለበት፣ በተለያዩ ጎራዎች የተሰለፉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ህይወት ዶጋ አመድ አድርጎ ግንቦት 20, 1983 ዓ.ም የተቋጨው ጦርነት አንድን ወታደራዊ አምባገነን መሪ በኃይል በማስወገድ የይምሰል ዴሞክራሲያዊ ስርአትን(pseudo democracy) የገነባ ሲቪል አምባገነን መተካት የተወሰነ ቡድንን ወይም ግለሰቦችን ፖለቲካዊ የበላይነት(hegemony) ለማረጋገጥ ያለመ እንዳልነበር በትጥቅ ትግሉ ተሳታፊ የነበሩ ግለሰቦች ያረጋግጣሉ፡፡ የህወሓት ነባር ታጋይና የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ገብሩ አስራት ሰኔ 19,2002 ለወጣችው አዲስ ፕሬስ ጋዜጣ አሞራው ስለተባለ የህወሓት ጀግና ታጋይ ሲያስረዱ ‹‹አሞራው ቀና ብሎ እየተደረገና እየሆነ ያለውን ነገር ቢያይ ይገርመው ነበር›› ካሉ በኋላ የአቶ መለስ መንግስት በአሞራውና በሌሎች ታጋይ ሰማእታት መስዋዕትነት ስልጣን እየነገደ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣን የያዘበት ተመሳሳይ ወቅት አምባገነናዊ ኮሚኒስት ስርአቶችን በማስወገድ ዴሞክራሲያዊ ግንባታ የጀመሩት የምስራቅ አውሮፓ ሀገራት በአጭር ጊዜ ውስጥ አመርቂ ለውጥ ማምጣታቸውን Carleton University፡ Institute of European and Russian Studies  አጥኚ የሆኑት ድራጎስ ፖፓ (DRAGOS POPA) ሮሜኒያንና ቡልጋሪያን ነቅሰው ያመላክታሉ፡፡ የባልካን ሀገራትም ሁለት አስርት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ እምርታ ማምጣታቸውን  The democratic transformation of the Balkans በሚል ርዕስ የቀረበው የሮዛ ባልፈር እና ኮሪና ስትራቱላት (Rosa Balfour and Corina Stratulat) ጥናት ያመላክታል፡፡  ጥናቱ የባልካን ሀገራት በአጭር ጊዜያት ውስጥ ሶስት መሰረታዊ ለውጦችን ማስመዝገባቸውን ያስረዳል‹‹ከጦርነት ወደ ሰላም፣ ከኮሚኒዝም የእዝ ኢኮኖሚ ወደ ነፃ ገበያ እንዲሁም ከአንድ ፓርቲ አገዛዝ ወደ መድብለ ዴሞክራሲ ተለውጠዋል›› ይላል፡፡ በዚህ ረገድ በኢትዮጵያ ባለፉት 21 አመታት የታየውና አሁንም ያለው ነባራዊ ሁኔታ ለግንቦት 20 ድል የወጣውን  የህይወት ግብር እና በድሉ ማግስት የተገኘውን የግንቦት 20 ፍሬ ስናወራርድ ውጤቱ ኪሳራን የሚያመላክት ነው፡፡

ይህ ጽሁፍ በህወሓት በስተመጨረሻም በህወሓት/ኢህአዴግ መሪነት ለ17 አመታት በተደረገው ፅኑ ትግል የተገኘው የግንቦት 20 ድል ሊያመጣ ያልቻላቸውን አስር አንኳር ነጥቦች ይፈትሻል፡፡    Continue reading

ከ21 ዓመት በኋላ (ዴሞክራሲ ሲሰላ)

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ 'በ' - ጉብጠትኢሕአዴግ ከ21 ዓመታት በኋላ በዴሞክራሲ ጎዳና ወደኋለ መመለሱን ለማረጋገጥ ጥናት አያስፈልገውም፡፡ ታሪክን ባጭሩ ‹‹መገረብ›› በቂ ነው፡፡ ሆኖም ከሰሞኑ የተሰራች ትንሽዬ ቅኝትም የምንገርበውን የታሪኩን ወቅታዊ ደረጃ ውጤት ታረዳናለች፡፡

ኢሕአዴግ በትጥቅ ትግል አምባገነኑን ደርግ ከገረሠሠ በኋላ የሽግግር መንግስት አቋቋመ፡፡ የሽግግር መንግስቱ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን፣ በነፃ ሐሳብ የመግለፅ መብትን እና ወዘተ ዴሞክራሲያዊ መብቶችን የሚደነግገውን ሕገ መንግስት ቀረፀ፡፡

በታሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተሳተፉበት ምርጫም (ከነእንከኑ) ተካሄደ፣ ተደገመ፡፡ በርካታ የግል ጋዜጦች ተከፈቱ፣ ብዙ ሰዎችም ትንፋሽ ታፍኖ ከሚኖርበት የደርግ የኑሮ ዘዬ በከፊል በመላቀቅ ለመብታቸው ጥብቅና መቆም እና ሐሳባቸውን መግለፅ ጀመሩ፡፡ በዚህ መሃል ሦስተኛው ብሔራዊ ምርጫ (97) መጣ፡፡ ያ ወቅት የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ከፍተኛ ጫፍ (maximum peak) ላይ የደረሰበት ወቅት ነበር፡፡

ምርጫ 97 መጨረሻው ብጥብጥ ሆነ፡፡ ከዚያ በኋላ እያቆጠቆጠ የነበረው ሕዝባዊ ነፃነት እና ዴሞክራሲ ወደአፎቱ ተመለሰ፡፡ ኢሕአዴግም በኢትዮጵያ ታሪክ በምርጫ ስልጣን በመልቀቅ አዲስ ምዕራፍ የመክፈት ዕድሉን በገዛ ፈቃዱ ገደለው፡፡ በርካታ አዋጆች የዴሞክራሲያችንን አቅም፣ የሕዝቡን ነፃነት እና እምነት አሽመደመዱት፡፡

ዛሬ መንግስት ዴሞክራሲን እያሳደገ እንደሆነ ቢናገርም፡፡ እስካሁን ድረስ በሕገመንግስቱ የተቀመጡት መብቶች ባይፋቁም ተግባራዊነታቸው ግን ወደ 1983 ተመልሶ ‹በ› ጉብጠት (n-curve) ሰርቷል፡፡ Continue reading